እንተዋወቅ

ቴክኖ አዲስ መፅሄት በህዳሴ የህትመትና ማስትወቂያ ስራ ህ/ሽ/ማህበር የሚታተም በሀገራችን ኢትዮጲያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ፣ምርምሮች ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች የቢዝነስ ፣ የጤና፣ የመዝናኛ፣ የስፖርት እንዲሁም ጥናታዊ መረጃዎች ዙሪያ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚታተም መፅሄት ነው ፡፡

ቴክኖ አዲስ መስከረም 2007 ዓ.ም በመገናኛ ብዙሀንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥ 590/2000 አንቀፅ9/1 መሰረት በኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሞያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና እውቅና ያገኘ የሚዲያ ተቋም ነው ፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት በሚጠቅም መልኩ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርትና በኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ዙሪያ ከሚሰሩ የመንግስትና የግል ተቋሞች ጋር በጋራ ይሰራል

ቴክኖ አዲስ ሚዲያ በመፅሄት ህትመት ብቻ ሳይሆን በዌብሳይት ፣ በኤፍ ኤም ሬዲዮ፣በቲቪ ሾው እንዲሁም በጥናትና ምርምር ማእከል ላይ ትኩረት የሚያደርግ የሚዲያ ተቋም ነው ፡፡

ለሃገራችን ኢትዮጲያ እድገት በጋራ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ መልእክታችንን አስተላልፋለሁ፡፡

ዓለም በተለያየ ጊዜ የተለያዩ እና ብዙ ክስተቶች ታስተናግዳለች እያስተናገደችም ትገኛለች፡፡ ከእነዚህ ትልልቅ ክስተቶች አሁን ላለንበት ዘመን እርስ በራስ ተሳስረው አንዱን ሌላውን በመተካካት ከእርሻ ዘመን (Agricaltural generation) ወደ ኢንዱስትሪ ዘመን (industrial generation) ከዚያም ተሻግሮ አሁን ላለንበት ዘመነ ኢንፎርሜሽን (information generation) ደርሰናል፡፡ ከዚህ ሽግግር ለሰው ልጅ አኗኗር አመቺ ሁኔታ በመፍጠር ብዙ መልካም ውጤቶች አሳይተዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አሉታዊ የሆኑ ውጤቶችም ተከስተዋል፡፡ ይህም አንዱ የሽግግር (Transformation) ባህሪ ሆኖ ይስተዋላል እነዚህ ክስተቶችም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ ማህበራዊ ግንኙነቶች በግለሰብም ሆነ በሀገር ደረጃ በበጎ መልኩ የመጡ ለውጦች አሁን ላለንበት በተለይ ሃገራችን እየተራመደችው ካለ የሽግግር ጉዞ እንዚህን መልካም ለውጦች ወይም ክስተቶች ለመቆናጠጥ መሪ ተዋናይ ሆናለች፡፡

ኢንፎርሜሽን የተጣራም ይሁን ያልተጣራ መረጃ መሠረታዊ የደም ሥር እስከመሆን የደረሰበት ዘመን ሲሆን ከዚህ በመነሳትም አለማችን በየዕለቱ ውስብስብ እና ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የመረጃ መለዋወጫ መተላለፊያ፣ መቀበያ፣መተንተኛ፣ማጠናከሪያ፣ቁስ ነገሮች ይመረታሉ፡፡ እነዚህም ውጤቶች በሚዲያ የሚካተቱ ሲኖሩ ከእነዚህም በሃገራችን ከሚገኙ የብሮድካስት ፣የኤሌክትሮ ሚዲያ እንዲሁም የተለያዩ የጽህፈት ውጤቶች ናቸው፡፡ በሃገራችን ብቸኛ የሆነው ይህ መጽሔት ቴክኖ አዲስ በሚል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

Our company HPPWP/technoaddismedia provide services

1. All Printing works
2.digital Marketing Promotion
3. Media event coordination and All media advertisement services
4. Any kind of documentary movies making
5. web site development , hosting and Camera security installations.

       ውድ አንባብያን

ቴክኖ አዲስ በአለም አቀፍ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ እና የሚከናወኑ የቴክኖሎጂ ሂደቶች፣ ምርቶች፣ የመረጃ አጠቃቀም የመረጃ አያያዝና ጥንቃቄ አስተማማኝ እና ውጠየታማ ለማድረግ እንዲሁም ይህ አዲሱ ትውልድ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው፤ መንግስት እና ህዝብ በቴክኖሎጂው አጠቃቀምና አያያዝ ያሉበትን ክፍተቶች በመለየት እና መፍትሔዎችን በመጠቆም ሀገራችን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የአስተሳሰብ ነጻነት በኢኮኖሚ የዳበረች በፖለቲካ የተረጋጋች ትልቅ ሃገር ሆና እንድትቀጥል በሚያስችል የበኩላችንን ሃገራዊ (ዜግነታዊ) ግዴታ የምትወጣ መጽሔት እንድትሆን እንመኛለን፡፡ ውድ አንባብያንም ይህንን የጋራ የትልቅነት ራዕይ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እና ድጋፍ በማድረግ አብረን ወደ ትልቅነት እንጓዝ፡፡

Close Menu